This page contains information about Office of Unified Communications services for Amharic speakers.
የኤጀንሲው ስም፡ የተቀነባበረ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ( Office of Unified Communications )
ተልእኮ
የተቀነባበረ ኮሚኒኬሽን ቢሮ (Office of Unified Communications (OUC) ራእይ በዲስትሪክቱ ፈጣን፤ ሞያዊ እና ወጪን- ያማከለ፤ የአደጋ (911) እና የአደጋ ላልሆኑ የከተማ አገልግሎት ጥሪዎችን (311) ምላሽ መስጠት ነው። በተጨማሪም፣ ኦዩሲ(OUC) የህዝብ ደህንነት የድምጽ ራዲዮ ቴክኖሎጂ እና ሌሎች የህዝብ ደህንነት ሽቦ-አልባ፤ የመረጃ ኮሚኒኬሽን ሲስተም እና መረጃዎች ላይ፤ የተማከለ ጠቅላላ ዲስትሪክቱን ያካተተ የማስተዳደር እና የማቀነባበር አገልግሎትን ይሰጣል።
ስለ ክፍሉ
911 - ፖሊስ፤ እሳት እንዲሁም የድንገተኛ ግዜ የህክምና አገልግሎት ሲፈልጉ 911 ይደውሉ። 911 መደወል ከክፍያ ነጻ ነው፤ እንዲሁም ከማንኛውም የዲስትሪክቱ ቦታ ሆነው ከመኖሪያ ቤት፤ ከሽቦ-አልባ እና ከህዝብ ስልኮች ሊደወል ይችላል። ከታች የተጠቀሱትን ለመጠቆም 911 ይጠቀሙ፡-
- ማንኛውንም በሂደት ላይ ያለ ወንጀል ወይም ጥፋተኛው በአካባቢው ካለ (ወይም ወድያው አካባቢውን እንደለቀቀ)
- ሁሉም የእሳት እና የህክምና አደጋዎች
- የቤት እና የስራ ደፋሪዎች(ሰርጎ-ገቦች)
- በሰው ላይ ጉዳት፣ ከፍተኛ የንብረት መውደም ወይም የትራፊክ መጨናነቅ ያደረሱ የመኪና ግጭቶች
- በፖሊስ እንደሚፈለግ የሚያውቁት ወንጀለኛ ባዮ ግዜ
311 - የስልክ ማእከል አገልግሎቱ (Call Center Operation)፣ የከተማ አገልግሎቶችን፤ ቁጥሮችን እና መርጃዎችን ለሚፈልጉ ለአባላት፣ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች የፈጣን እና ሙሉ አገልግሎት (one-stop service) ልምዱን ይሰጣል። አገልግሎቱ የተዘጋጀው ህዝቡ ከከተማው መንግስት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ሲል ያሚገጥመው ክብደት እንዲቀንስ ነው። እንደ ቆሻሻ ለማንሳት፣ የመንገድ ጉድጘዶችን ለመጠገን ፣ የተጠራቀመ ቆሻሻ ማስነሳት እና ሪሳይክል የሚሆኑትን መሰብሰብ ለመሳሰሉ አገልግሎቶች ቀጠሮ ለማስያዝ 311ን መጠቀም ይቻላል። በተጨማሪም፣ የ311 ደዋዮች በቀጠሮ ያልተገኙ የጽዳት አገልግሎቶችን ለመጠቆም፤ የከተማ ኤጀንሲ የስልክ ቁጥሮችን እና የስራ ሰአቶችን ለመጠየቅ እና ሌሎች የደንበኛ-አገልግሎት-ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ለማግኘት ቁጥሩን መጠቀም ይችላሉ።
311 እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
1. 3-1-1 በቀን 24 ሰአት፣ በአመት 365 ቀናት ይደውሉ
2. ጥያቅይዎችን በ311ህብረመረቡ መስመር(311Online)(www.311.dc.gov)ያቅርቡ
3. የዲሲ311 ስማርት ፎን አፕ( DC311 Smartphone App) ከህብረመረብ ያውርዱ(download)
አገልግሎቶች :-
ዲሲ311(DC311) - በዋነኝነን የተዘጋጀው የከተማውን አገልግሎት መጠየቅን የበለጠ አመቺ ለማድረግ፤ የዲሲ311 አፕ(DC311 app) ህብረተሰቡ ችግሮችን ወዲያውኑ ከዚያው ከቦታው እንዲያመለክቱ፣ የችግሮቹን ፎቶግራፎች እንዲያይዙ፣ እንዲሁም የጠየቁት ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እዳለ እንዲከታተሉ የሚያስችላቸው በዚየኑ ሰአት የሚሰራ (real time) መሳሪያ ነው። ቆሻሻን መሰብሰብ፤ የተበላሸ መንገድ መጠገን፤ ህገ-ወጥ የግድግዳ ጽህፈት(ስእል) ማጥፋትን ጨምሮ ከ80 በላይ የተለያዩ አገልግሎቶች መሀኸል መምረጥ ያስችላል። የስማርተት ፎን( smartphone) አገልግሎቱ ነጻ ነው፣ እናም በሁለቱም አይ ፎን እና በአንድሮይድ ሞባይል መጠቀም ያስችላል።
ስማርት911(Smart911) - የተቀነባበረ ኮሚኒኬሽን ቢሮ(Office of Unified Communications) የ911 አገልግሎትን ለነዋሪቹ ለማሻሻል፣ ስማርት 911ንን በጁላይ 2012 በዋሽንግተን ዲሲ አስተዋወቀ። ተጠቃሚዎች ድንገተኛ የአደጋ እርዳታ ቢያስፈልጋቸው የመጀመሪያ ደራሾች እንዲኖረቸው የሚፈልጉትን ማንኛውንም መረጃ የሚያካትት ለቤታቸው የደህነቱ መረጃን(Safety Profile) ለማዘጋጀት የሚያስችላቸው የነጻ አገልግሎት ነው። ከዚያም፣ ከደህንነት መረጃው(Safety Profile) ጋር ከተያያዘ ስልክ 9-1-1 ሲደወል የመረጃው ማህደሩ ወዲያውኑ ለ911 ስልክ ተቀባዩ ይከፈታል። ማህደሩ ለስልክ ተቀባዩች ወሳኝ የሆነ መረጃ በመስጠት አግባብ ያለው ምላሽ በትክክለኛው ቦታ ላይ እዲሰጥ ለማስተባበር ያስችላቸዋል። ለቤትዎ የደህንነት መረጃን (Safety Profile) እዚህ ይክፈቱ www.smart911.com ።
የትርጉም አገልግሎት:-የኦዩሲ (OUC) ሰራተኞች በስፓኒሽ፣ ጣሊያንኛ፣ ኮሪያን፣ ፋርሲ እና ሌሎች በርካታ ቐንቐዎች የደንበኞች አገልግሎት ይሰጣሉ። ከላንጉጅ ላይን አገልግሎት እርዳታ በማግኘት፣ ኤጀንሲው ቢያንስ ለ200 ተጨማሪ ቐንቐዎችገ የትርጉም አገልግሎት ይሰጣል።
አድራሻ፦
DC Office of Unified Communications 2720 Martin Luther King Jr. Ave, SE Washington DC 20032
202-730-0524. ለማህበረሰብ ግኑኝነት(outreach) ወይም ሚዲያ ጥያቄዎች [email protected] ን ያግኙ ወይም በ 202-730-0503 ይደውሉ። ኦዩሲ (OUC)ን በትዊተር Twitter @311DCgov ይከተሉ።